ሲዳማ ቡና ወደ ሊጉ መሪነት ለመመለስ ከሸገር ከተማ ጋር ይጫወታል።

0
32
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 21/2018ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሲዳማ ቡና መሪነቱን መረከብ የሚያስችለውን ድል ለማስመዝገብ ከሸገር ከተማ ጋር ይጫወታል።
ሲዳማ ቡና በሊጉ ካደረጋቸው 11ጨዋታዎች 22 ነጥብ በመሠብሠብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቡድኑ ትናንት ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን በማሸነፉ የነጠቀውን የመሪነት ደረጃ ለማስመለስ ምሽት 12:00 በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ነው ከሸገር ከተማ ጋር የሚጫወተው።
ተጋጣሚው ሸገር ከተማ ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች 12 ነጥብ እና ሁለት የግብ ዕዳ በመያዝ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ በሊጉ ካደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው። ይህም የቡድኑን የመከላከል እና የማጥቃት መስመር መዳከም ያሳያል።
ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጫወቱ ይኾናሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here