በታሪክ ብዙ የቦክሲንግ ዴይ ድል ባለው ማንቸስተር ዩናይትድ እና ብዙ የሽንፈት ታሪክ ባለው ኒውካስል መካከል የሚደረገው የዛሬው ጨዋታ።

0
47
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 17/2018 ዓ.ም አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የገና ጨዋታ ወይም የቦክሲንግ ደይ ጨዋታ እያሉ ይጠሩታል የገና ሰሞን የበዓል ጨዋታዎችን።
ይህ ጨዋታ ታዲያ በአንጋፋው እና ብዙ ተመልካች ባለው የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኒውካስል ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ይጀመራል።
ይሁን እንጅ ዩናይትድ አሁን ላይ ከኒውካስል ጋር ባለው ፉክክር እና ወቅታዊ አቋሙ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አራቱን በመሸነፉ ኒውካስል በዩናይትድ ላይ የበላይነትን አሳይቷል።
ኦልድ ትራፎርድ ዛሬ ኒውካስልን በማሸነፍ ታሪክ ካልቀየረ በቀር ባለፈው የውድድር ዘመን በዩናይትድ ላይ የደርሶ መልስ ድል የቀናው ኒውካስል አሁንም ተከታታይ ድል ለማስመዝገብ የሚችልበት ዕድሉ ሰፊ ነው።
ዛሬ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ በቦክሲንግ ዴይ መጀመሪያ ላይ አንድ ጨዋታ ብቻ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው። በዚህም ታሪክ የሚጽፉት ቡድኖቹ ዓለም ዐይኖቹን እንዳሳረፈባቸው ድልን አጣጥመው ታሪክ ለመጻፍ ከበድ ያለ ፍልሚያ ያደርጋሉ።
ጨዋታው በታሪክ 22 ጊዜ የቦክሲንግ ዴይ ድል ባለው ማንቸስተር ዩናይትድ እና 16 ጊዜ ሽንፈት ባለው ኒውካስል መካከል የሚደረግ ሲኾን ይህን ታሪክ ለመቀየር እና ለማስቀጠል ባለው ፍትጊያ ጨዋታው ይካሄዳል።
ዩናይትድ በቦክሲንግ ዴይ ከኒውካስል ጋር በ2012፣ 2014 እና 2019 ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ማሸነፉን ታሪክ ያስታውሰናል ቁምነገሩ ዛሬስ የሚለው ይኾናል?
የትኛውንም ጨዋታ የማሸነፍ አቅም አለን ሲሉ ሩበን አሞሪም ሀሳብ መስጠታቸው ለዩናይትድ ደጋፊዎች ትልቅ የሞራል ማነቃቂያ ተደርጎ ተወስዷል።
በርካታ ተጫዋቾቻውን በጉዳት አጥተው ኒውካስል ዩናይትድን የሚገጥሙት የማንቸስተር ዩናይትዱ አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም የትኛውንም ጨዋታ የማሸነፍ አቅም አለን ሲሉ ነው የተደመጡት።
ዛሬ በሚካሄደውም የቦክሲንግ ደይ ጨዋታ ተከላካዮቹ ሃሪ ማጉዋየር እና ማቲያስ ዴሊክን ጨምሮ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ እና ኮቤ ሜይኖ በጉዳት ከጨዋታው ውጭ ናቸው።
ይሁን እና ለአካዳሚ ልጆች ዕድል እየሰጡ የሚገኙት አሠልጣኙ ባላቸው ሥብሥብ ዕምነት እንዳላቸው እና የትኛውንም ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚችሉ ከጨዋታው አስቀድመው እየተናገሩ ይገኛሉ።
አሠልጣኙ ቡሩኖ እና ሜይኖ ከጉዳት እያገገሙ መኾናቸውን ገልጸው ሜይኖ በአጠረ ጊዜ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ መናገራቸውን ስካይ ስፖርት አስነብቧል። ጨዋታውም ዛሬ ምሽት 5፡00 ይካሄዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here