በአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን፣ አይቬሪኮስት፣ አልጀሪያ እና ቡርኪናፋሶ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ።

0
39
ሕር ዳር: ታኅሣሥ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ በተካሄዱ አራት ጨዋታዎች ምድብ አምስት ላይ የምትገኘው አልጄሪያ ሱዳንን 3ለ0 አሸንፋለች።
በዚሁ ምድብ የሚገኙት ቡርኪና ፋሶ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ያደረጉት ጨዋታ በቡርኪናፋሶ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዚህ ምድብ አልጀሪያ እና ቡርኪና ፋሶ በእኩል ሦሥት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ምድባቸውን እየመሩ ነው። ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ሱዳን ደግሞ ያለነጥብ በምድቡ ሰንጠረዥ ተቀምጠዋል።
ምድብ ስድስት ላይ የምትገኘው ኮትዲቯር (አይቮሪ ኮስት) ሞዛምቢክን 1ለ0 አሸንፋለች።
በዚሁ ምድብ ካሜሩን እና ጋቦን ያደረጉት ጨዋታ በካሜሮን 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ምድቡን አይቬሪኮስት እና ካሜሮን በሦሥት እኩል ነጥብ በግብ ከፍያ ተበላልጠው እየመሩ ነው። በዚሁ ምድብ ጋቦን እና ሞዛምቢክ ያለምንም ነጥብ ተቀምጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here