አጓጊው ደርቢ…

0
42
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ የአማራ ክልል ተወካዮች እርስ በእርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 10:00 ይደረጋል።
ፋሲል ከነማ እስካሁን 10 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ንጹህ የግብ ክፍያ በመያዝ እና 20 ነጥብ ሠብሠቦ ከመሪው ሲዳማ ቡና በአንድ ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ በሁለተኛነት ተቀምጧል።
ቡድኑ በሊጉ ባደረጋቸውን ጨዋታዎች አልተሸነፈም፤ ይህም የአጼዎቹን ጥንካሬ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ፋሲል ከነማ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈም የሊጉ መሪ ይኾናል።
ባሕር ዳር ከተማ በበኩሉ ከ10 ጨዋታዎች 13 ነጥብ በመያዝ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የጣናው ሞገድ በሊጉ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር በሸገር ከተማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ዋንጫ ደግሞ በቦዲቲ ከተማ ተሸንፏል።
በ10ኛ ሳምንት ደግሞ ከምድረ ገነት ሽረ ጋር ያደረገውን ጨዋታ የፍጹም ቅጣት ምት በመሳት ዜሮ አቻ ተለያይቷል።
ቡድኑ በአጠቃላይ የማሸነፍ ተነሳሽነቱን በወጥነት ማስቀጠል አልቻለም፡፡
ዛሬ ፋሲልን የሚያሸንፍ ከሆነም ደረጃውን ወደ ስድስተኛ ከፍ ያደርጋል።
በሌሎች ጨዋታዎች ቀን 7:00 ነገሌ አርሲ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9:00 አርባ ምንጭ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ እንዲሁም ምሽት 12:00 ሀዲያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ዘጋቢ፦ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here