ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ በጅማ እና ሐዋሳ ከተሞች ቀጥሎ ይውላል።
በሊጉ ምድብ “ለ” ላይ የተደለደለው የአማራ ክልል ተወካዩ ደሴ ከተማ እስካሁን ሰባት ጨዋታዎችን አድርጓል። ሦስት የግብ ክፍያ እና 10 ነጥብ በመያዝ አራተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው።
ቡድኑ ዛሬ በስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በጅማ ስታዲየም ቀን 7:00 ላይ ከምድቡ መጨረሻ ከሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ጋር ይጫወታል።
ቡድኑ አንዴ ሲያሸንፍ ሌላ ጊዜ አቻ ይለያያል፤ መገለጫው ደግሞ ከሶሎዳ ዓድዋ ጋር ዜሮ ለዜሮ እንዲሁም ከቢሾፍቱ ከተማ ጋርም አንድ አቻ በመለያየት፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማን ደግሞ 2ለ0 አሸንፏል።
የቡድኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር አብርሃም ተስፋ ለአሚኮ እንዳሉት የሚያደርጉት የተቀናጀ ዝግጅት ፕሪምየር ሊግ መቀላቀልን ታሳቢ ያደረገ ነው። ለዛሬው ጨዋታም ጥሩ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።
የደሴ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን በመከላከሉ ረገድ አቅሙ ከፍተኛ መኾኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።
ቡድኑ ወጥ አቋም ያልያዘው ወሳኝ እና ጨራሽ የኾኑ ተጨዋቾችን በቅጣት ምክንያት ማሰለፍ ባለመቻሉ እንደኾነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ዛሬ ግን ቅጣት ላይ የነበሩ ተጨዋቾች በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ስለተካተቱ አሸንፈው ደረጃቸውን ወደ መሪነቱ ለመጠጋት እንደሚጫወቱ ነው የገለጹት።
በጅማ እና አካባቢው የሚገኙ ደጋፊዎችም የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቅኝቶቹ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ከመሪዎች ተርታ መጠጋት ይችላሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



