ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 36 ቡድኖችን እያፎካከረ የሚገኘው የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታ ስድስተኛ ዙር ዛሬ ምሽት 5:00 ላይ በ18 ከተሞች ቀጥሎ ያመሻል።
በሊጉ አምስት ጨዋታዎችን በማድረግ 13 ነጥብ በመሠብሠብ ቀዳሚ የኾነው የፈረንሳዩ ስትራስቡርግ ከአይስላንዱ ብሬዳብሊክ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ስትራስቡርግ ጨዋታውን ካሸነፈ መሪነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል። 12 ነጥብ በመያዝ በሁለተኛነት የተቀመጠው የዩክሬኑ ሻክታኽር ዶኔትስክ ከክሮሽያው ራጅካ ጋር የሚያከናውነው ጨዋታ የምሽቱ ሌላ ተጠባቂ ጨዋታ ነው።
ሻክታር ዶኔትስክ በጨዋታው አሸንፎ ስትራስቡርግ ከተሸነፈ መሪነቱን መረከብም ይችላል። በ11 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ በሦሥተኛነት የሚገኘው የፖላንዱ ራካዎ እና የሩማኒያው ኦሞኒያም ምሽት 5:00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታም የደረጃ ለውጥን ያስከትላል።
10 ነጥብ በመያዝ በአራተኛነት የተቀመጠው የግሪኩ ኤ.ኢ.ኬ አቴንስ ከሩማኒያው ዪ ክራሎቫ ይገናኛል። በተመሳሳይ ክሪስታል ፓላስ ከ ኩፐስ፣ ዳይናሞ ኬይቭ ከ ኖዓህ፣ ሉውሰኔ ከ ፊዮሪንቲና፣ ሜንዝ 05 ከ ከሳምሱንስፐር፣ ስፓርታፕራግ ከ አቤርዲን ምሽት 5:00 ላይ ከሚደረጉ 18 ጨዋታዎች መካከል ይገኙበታል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



