ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በካራባኦ ዋንጫ ዛሬ ምሽት 4:45 ማንቸስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ በኢትሃድ ስታዲየም ይጫዎታሉ፡፡
ማንቸስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ እንደ ሃላንድ እና ፎደን ብሬንትፎርድ ደግሞ እንደ ቲያጎ የመሰሉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋቾችን የያዙ በመኾናቸው ጨዋታው ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሏል፡፡
የዜጎቹ አሠልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ ራያን አይት ኑሪ እና ኦማር ማርሙሽ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማቅናታቸውን ተናግረዋል፡፡ ጄርሚ ዶኩም በጉዳት እስከ ሦስት ሳምንታት ድረስ ጨዋታዎች ያልፉታል ነው ያሉት፡፡ ኾኖም እነዚህ ተጨዋቾች የሚተኩ ሌሎች ተጨዋቾች ስላሉ ለእነርሱ ዕድል እንደሚሰጡ ነው ያብራሩት፡፡
የብሬንትፎርድ አሠልጣኝ ኪት አንድሪውስ ለቢቢሲ እንዳሉት ከጠንካራው ማንቸስተር ሲቲ ጋር መጫወት በጣም አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡
በስብስብ ረገድ ናይጀሪያዊው አማካይ ፍራንክ ኦንያካ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መሄዱን የጠቆሙት አሠልጣኙ የቡድኑ የማሸነፍ ሥነ ልቦና ከፍተኛ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
በሌላ ጨዋታ ምሽት 5:15 ኒውካስትል ዩናይትድ እና ፉልሃም በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡
ዘጋቢ:- ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



