የዩሮፓ ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች፦

0
10

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዩሮፓ ሊግ ስድስተኛ ዙር መርሐ ግብሮች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች 18 ጨዋታዎች ይከናወኑበታል። ኦሊምፒክ ሊዮንስ ከጎ ኤሄድ ኤግልስ፤ ሚችያላንድ ከጌንክ፣ አስቶን ቪላ ከባዜል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የፈረንሳዩ ኦሊምፒክ ሊዮንስ የዩሮፓ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥን እየመራ ነው። ዛሬ 27ኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው የኔዘርላንዱ ከጎ ኤሄድ ኤግልስ ጋር ምሽት 5፡00 ላይ ይጫወታል። ኦሊምፒክ ሊዮንስ እስካሁን ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች በአራቱ አሸንፎ እና በአንዱ ተሸንፎ 12 ነጥብ በመሠብሠብ ነው የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራ የሚገኘው።

ተጋጣሚው የኔዘርላንዱ ጎ ኤሄድ ኤግልስ ደግም ከአምስት ጨዋታዎች በሦስቱ ተሸንፎ 27ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የዴንማርኩ ሚትላንድ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው የቤልጅየሙ ጌንክ ምሽት 2:45 ይጫወታል።
ሦሥተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የእንግሊዙ አስቶን ቪላ ምሽት 5:00 ወደ ስዊዘርላንድ አምርቶ ከባዝል ጋር ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋል።

አስቶን ቪላ እስካሁን ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች የተሸነፈው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። 12 ነጥብ በመሠብሠብም በግብ ክፍያ ተበልጦ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የኤምሬው ቡድን ዛሬ ማሸነፍ ከቻለና በደረጃ ሰንጠረዡ መሪነት ላይ የተቀመጡ ክለቦች ከተሸነፉ ወደ መሪነት የመምጣት ዕድል ይዞ ጨዋታውን ያደርጋል።
ምሽት 2:45 ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከልም፦
👉ዳይናሞ ዛግሬብ ከሪያል ቢትስ፣
👉ፈረንቺቫሮስ ከሬንጀርስ፣
👉ሉዶጎሬትስ ከፓኦክ፣
👉ኔንይስ ከስፖርቲንግፕራጋ፣
👉ስቱርም ግራዝ ከሬድስታር ቤልግሬድ፣
👉ስቱትግራት ከማካቢ ቴል አቪቭ፣
👉ዩትሬክት ከኖቲንግሃም ፎሬስት፣
👉ያንግ ቦይስ ከሊል ይጫወታሉ።
ምሽት 5 ሰዓት ደግሞ
👉ብርነን ከፌነርባቼ፣
👉ሴልታ ቪጎ ከቦሎኛ፣
👉ሴልቲክ ከሮማ፣
👉ኤፍሲኤስቢ ከፌይኑርድ፣
👉ፍሪቡርግ ከሬድ ቡል ሳልዝቡርግ፣
👉ፓናቲናይኮስ ከቪክቶሪያ ፕላዛን እና
👉ፖርቶ ከማልሞ ጨዋታቸውን አንደሚያደርጉ ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here