የዶሃ ፎረም ለአትሌቲክስ መሠረተ ልማት

0
13
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2019 ድንቅ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ያስተናገደችው ዶሃ ወዲህ ደግሞ መልካም ዜናን እንካችሁ ብላለች።
ትላንት በኳታር ዶሃ ለሦስት ቀናት የቆዬ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከታኅሣሥ 6 እስከ 8 ድረስ “የዶሃ ፎረም” የተሰኘ መድረክ የተከናወነ ሲኾን ዓለም አቀፍ ዴሞክራሲ ላይ ትኩረቱን ያደረገም ነበር።
በዚህ መድረክ የኳታር ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የዓለም አትሌቲክስ ከኳታር የልማት ፈንድ ጋር በመተባበር ወሳኝ ተግባርን ለማከናወን ተስማምቷል።
በስምምነቱ በአትሌቲክስ ስፖርት የመሰረተ ልማት ግንባታ እጥረት አለባቸው ተብለው በተመረጡ 11 ሀገራት የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ነው ስምምነት ላይ የደረሱት።
በአራት አህጉራት በሚገኙ 11 ሀገራት ማለትም ከአፍሪካ ታንዛኒያ እና ቡሩንዲ፣ ከምሥራቅ አውሮፓ ሞልዶቫ እና ዩክሬን፣ ከመካከለኛው አሜሪካ ፓናማ፣ ከመካከለኛው እስያ ካይጊስታን እና ታጃኪስታን እንዲሁም ከደሴት ሀገራት አንጉይላ ኩክ አይስላንድ እና ዶሚኒካ በተጨማሪም ፍልስጤም ናቸው።
በእነዚህ ሀገራት የሚገነቡ የአትሌቲክስ የልምምድ ማዕከላት ሁለት ሁኔታዎችን ማሟላት ያለባቸው መኾኑንም መረጃው ያመላክታል።
ግንባታው ሲከናወን አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ እና የሚገነቡበት ቁሳቁስ ለአካባቢው የሚስማማ ወይም ከአየር ብክለት ነጻ መኾን አለበት ተብሏል።
በተለይም ይሄ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የልምምድ ቦታዎችን በማጣት በሩ ለተዘጋባቸው ወጣቶች ትልቅ እድልን የሚፈጥር እንደኾነም ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here