የጣና ሞገዶቹ ከሸገር ከተማ ዛሬ ይጫወታሉ።

0
27
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት 12፡00 የጣና ሞገዶቹ ከሸገር ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የጣና ሞገዶቹ በስምንተኛ ሳምንት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ተገናኝተው 1ለ0 ማሸነፋቸው የሚታወስ ሲኾን ይህኛውንም ጨዋታ አሸንፈው ወደፊት ለመጓዝ ዛሬ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
በሀዋሳ በሚደረገው በዚህ ጨዋታ የጣና ሞገዶቹ በ12 ነጥብ ካሉበት ስምንተኛ ደረጃ ለማሻሻል ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት።
ተጋጣሚያቸው ሸገር ከተማ ባለፈው ስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ ከነገሌ አርሲ ጋር ተገናኝቶ በሁለት አቻ ተለያይቷል።
ሸገር ከተማ በዘጠኝ ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክለብ ነው።
ቀደም ብሎ በተደረገ ሊጉ ጨዋታ ውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2ለ1 ሲያሸንፍ አዳማ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ 9፡00 ጀምረው እየተጫወቱ ነው።
ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ደግሞ 10፡00 ላይ ይጫወታሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here