ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በኋላ በአሜሪካ ይካሄዳል፡፡ በምድብ ድልድሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይታደማሉ ተብሏል።
አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በጋራ በሚያስተናግዱት የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል በዋሽንግተን ይፋ የሚደረግ ይኾናል፡፡
ከፕሬዝዳንት ትራምፕ በተጨማሪም የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ይታደማሉ።
የቀድሞው የእግር ኳስ ከዋክብት፣ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች እና ሌሎችም ወደ ዕጣ ድልድሉ መድረኩ እየገቡ መኾኑን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



