አርሰናል መሪነቱን ሲያጠናክር ቸልሲ ተሸንፏል፤ ሊቨርፑል ደግሞ አቻ ተለያይቷል።

0
80

ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ብሬንትፎርድን 2ለ0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

ለአርሰናል ሚካኤል ሜሪኖ እና ቡካዮ ሳካ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

መድፈኞቹ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ካለው ማንቸስተር ሲቲ በአምስት ነጥብ ርቀው መቀመጥም ችለዋል።

በሌላ የሊጉ ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ቼልሲን 3ለ1 አሸንፏል።

ሊቨርፑል ደግሞ ከሰንደርላንድ ጋር አንድ አቻ ተለያይቷል።

በሌሎች የምሽቱ ጨዋታዎች አስቶንቪላ ብራይተንን 4ለ3፤ ክርስታል ፓላስ በርንለይን 1ለ0 እና ኖቲንግሀም ፎረስት ወልቨስን 1ለ0 ረተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here