ግብጽ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኟን አሰናበተች።

0
280

ባሕርዳር: ጥር 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የግብጽ ብሔራዊ ቡድን በጥሎ ማለፉ መሸነፉ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም የቡድኑ አሠልጣኝ ሩይ ቪቶሪያ መሰናበታቸውን የግብጽ እግር ኳስ ማኀበር አስታውቋል።

ፖርቱጋላዊው ሩይ ቪቶሪያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኑን ለማሠልጠን የነበራቸው የስምምነት ውል የሚጠናቀቀው እንደ እውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2026 ነበር፡፡

ሰውየው ቡድኑን ከአፍሪካ ዋንጫ ባለፈ ለዓለም ዋንጫም እንደሚያሳትፉት ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር።ይሁንና ቡድኑ ከአፍሪካ ዋንጫ በጊዜ መሰናበቱን ተከትሎ ሩይ ውላቸው ሳይጠናቀቅ እንዲሰናበቱ።

የግብጽ እግር ኳስ ማኀበር የ53 ዓመቱን አሠልጣኝ ሩይ ቪቶሪያ ብቻ ሳይኾን ሌሎች የቡድኑን አሠልጣኞች እና መሪዎችን ጨምሮ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የሀገሪቱ እግር ኳስ ማኅበር አስታውቋል።

የዓል ዓሐሊ ቡድን የቀድሞ አሠልጣኝ መሐመድ የሱፍ በጊዜያዊነት ፈርዖኖችን እንዲያሠለጥኑ መወሰኑን ሮይተርስ ጨምሮ ዘግቧል፡፡ የቀድሞ የግብጽ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋች ዋኤል ጎማ ” በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለግብጽ ቡድን ውጤት መጥፋት ዋነኛው ተጠያቂ ቪቶሪያ ነው” ሲል ለቢን ስፖርት መናገሩን ሮይተርስ አስታውሷል፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here