ባሕር ዳር ከተማ ሲያሸንፍ ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋርቷል።

0
35
ባሕር ዳር: ኅዳር 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ መካሄድ ሲጀምር ባሕርዳር ከተማን ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያገናኘው ጨዋታ በባሕር ዳር ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግብ ከእረፍት መልስ መሳይ አገኘሁ አስቆጥሯል።
ሌላው በሊጉ በፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ የተካሄደው ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቅቋል።
ግቦቹን ፋሲል ከነማ በዳግም አወቀ አማካኝነት ሲያስቆጥር የወላይታ ድቻን ግብ መሳይ ሰለሞን አስቆጥሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here