ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጀርመን ቡንደስ ሊጋ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 12:30 ሰዓት ላይ ባየር ሊቨርኩሰን ከቦሩሲያን ዶርትሙንድ ጋር ተጠባቂ ጨዋታን ያደርጋል፡፡
ባየር ሊቨርኩሰን ከ11 ጨዋታዎች ስድስቱን አሸንፏል፡፡ በአራቱ አቻ ተለያይቶ እና በአንዱ ተሸንፎ 23 ነጥብ በመሰብሰብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ጨዋታውን ካሸነፈ ደግሞ ደረጃውን ወደ ሁለተኛነት ከፍ ያደርጋል፡፡
ቦሩሲያን ዶርትሙንድ በአንጻሩ ከ11 ጨዋታዎች ሰባቱን ነው ያሸነፈው፡፡ በሁለቱ አቻ ተለያይቶ እና በሁለቱ ተሸንፎ 22 ነጥብ በመሰብሰብ አራተኛ ደረጃ ለይ ይገኛል።፡ጨዋታውን ድል የሚያደርግ ከኾነ ደረጃውን ወደ ሦስት ያሳድገዋል፡፡
በጣልያን ሴሪ ኤ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ደግሞ ኤሲ ሚላን ከላዚዮ ምሽት 4፡45 ሰዓት ላይ ተጠባቂ ጨዋታን ያደርጋል።
ኤሲ ሚላን እስካሁን 12 ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡ በሰባቱ አሸንፎ፣ በአራቱ አቻ ተለያይቶ እና በአንዱ ተሸንፎ 25 ነጥብ በመያዝ በሁለተኛነት ተቀምጧል፡፡
የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ መሪነቱን ከሮማ ይረከባል፡፡
ስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ላዚዮ የሚያሸንፍ ከኾነ ደረጃውን በአንድ ለማሻሻል ጁቬንቱስ ከካግሊሪያ ምሽት 2:00 ሰዓት ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ መጠበቅ ግድ ይለዋል፡፡
ቢቢሲን በመረጃ ምንጭነት ተጠቅመናል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



