ደሴ ከተማ ወደ መሪዎች መጠጋት የሚያስችለውን ጨዋታ ያደርጋል።

0
53
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የወንዶች እግር ኳስ የ2018 ዓ.ም መርሐ ግብር በሁለት ምድብ ተከፍሎ በጅማ እና ሃዋሳ ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል።
ምድብ “ለ” ላይ የተደለደሉት የአማራ ክልል ተወካይ ቡድኖችም ዛሬ በጅማ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቀን 7:00 ላይ ደሴ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ ይጫወታል።
ደሴ ከተማ እስካሁን ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች በአንዱ አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ ተለያይቶ እና በአንዱ ደግሞ ተሸንፎ በአራት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈም ወደ መሪ ቡድኖች የሚጠጋ ይኾናል። የደሴ ተጋጣሚ ቦዲቲ ከተማ በአንድ ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ደሴ ከተማ በባለፈው የውድድር ዓመት የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ኾኖ በመዝለቅ ፕሪሚየር ሊግ ገባ ሲባል በመጨረሻ በነገሌ አርሲ ተበልጦ ውድድሩን ማጠናቀቁ አይዘነጋም።
በሌላ ጨዋታ ቀን 9:30 ላይ ደብረ ብርሃን ከተማ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
ደብረ ብርሃን ከተማ እስካሁን ካደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ያለምንም ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here