ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በዛሬው ጨዋታ ታዲያ ተጠባቂ ሁለት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ስታዲየሞች ይካሄዳሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ፋሲል ከነማን ከድሬዳዋ ከተማ 10፡00 ላይ የሚያገናኘው ጨዋታ አንደኛው ነው። ባሕር ዳር ከተማን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ 12፡00 በሀዋሳ ስታዲየም የሚያገናኘው ሌላኛው ጨዋታ ነው።
በአምስት የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ጨዋታዎች 11 ነጥቦችን የሠበሠበው ፋሲል ከነማ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ነጥቡን ከፍ በማድረግ ደረጃውን ያሻሽላል።
እስካሁን ባደረጋቸው ጨዋታዎች ያልተሸነፈው ፋሲል ከነማ ዛሬ ከድሬዳዋ ጋር ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።
ባሕር ዳር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል። ጨዋታው በሀዋሳ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ ይካሄዳል።

ባሕር ዳር ከተማ በሊጉ አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ነጥቦችን ሠብሥቧል።
የጣና ሞገዶቹ የዛሬ ተጋጣሚ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ 11 ነጥቦችን ሠብሥቧል።
ምድረ ገነት ሽረ ከመቻል ቀን 7፡00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና አርባ ምንጭ ከተማ ከሸገር ከተማ ቀን 9፡00 በሀዋሳ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታም የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታ ነው።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



