ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ትጫወታለች።

0
15
ባሕር ዳር: ኅዳር 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ሦሥተኛ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል።
በምድብ አንድ የተደለደለችው ኢትዮጵያ ሦሥተኛ ጨዋታዋን ከሶማሊያ ጋር ታደርጋለች። ጨዋታው ዛሬ በአዲስ አበባ አበበ ቢቄላ ስታዲየም ቀን 10፡00 ላይ ይካሄዳል። ኢትዮጵያ በምድቡ ያደረገቻቸውን ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ በስድስት ነጥብ ምድቡን እየመራች ትገኛለች።
ተጋጣሚዋ ሶማሊያ በምድቡ ሁለት ጨዋታዎችን አድርጋ ሁለቱንም አቻ በመለያየት በሁለት ነጥብ ከምድቡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው የምትገኘው።
በሌላ ጨዋታ ኬኒያ ከሩዋንዳ ቀን 7:00 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ። ድሬዳዋ ላይም ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ጅቡቲ ከቡሩንዲ ቀን 10:00 ሲጫወቱ፣ ዩጋንዳ ከ ታንዛኒያ ምሽት 1:00 ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here