የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ክለቦች በጥር የተጫዋቾች ዝውውር 100 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ አውጥተዋል።

0
351

ጥር 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ክለቦች የጥር የተጫዋቾች ዝውውር ተጠናቋል። ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ያወጡት ወጪ 100 ሚሊዮን ፓውንድ መኾኑ ተረጋግጧል።ይህ ገንዘብ ከባለፉት ጊዚያት ጋር ሲወዳደር ዝቅተኛ መኾኑን ዴሎይት ስፖርት ቢዝነስ ግሩፕ በድረ ገጹ አስነብቧል።

ዘገባው ቡድኖቹ የፋይናንስን ሕግ በመጣስ በሚል ጠንከር ያለቅጣት እየተጣለባቸው በመኾኑ ለዝውውር ከፍተኛ ወጪ ከማውጣት ተቆጥበዋል ብሏል፡፡ ባለፈው ዓመት ኤቨርተን የፕሪሜየር ሊጉን የተጫዋቾች የዝውውር ወጪ ሕግን ጥሷል በሚል 10 ነጥብ እንደተቀነሰበት ለአብነት ተነስቷል፡፡

በመኾኑም በእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ የሚሳተፉ ቡድኖች በጥር ወር ለተጫዋቾች ዝውውር ያወጡት ወጭ ወደ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ወርዷል ብሏል፡፡ ክለቦቹ በጥር 2023 ለተጫዋቾች ዝውውር ያወጡት ገንዘብ 815 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር፡፡ ይህም በ2024 ጥር ወር ከወጣው አጠቃላይ ዋጋ በ715 ሚሊዮን ፓውንድ ያነሰ በመኾን በክብረ ወሰንነት ተመዝግቧል፡፡ በጥር 2024 የዝውውር ወቅት የወጣው ወጪ ዝቅተኛው መሆኑን ገልጿል፡፡

በጥር ወር 2024 ለተጫዋቾች ዝውውር የወጣው ወጪ ዝቅተኛ ቢሆንም በአጠቃላይ በፕሪሜየር ሊጉ እየተሳተፉ ያሉ 20 ቡድኖች በ2023/24 የውድድር ዘመን 2ነጥብ 5 ቢሊዮን ፓውንድ አውጥተዋል፡፡ ይህም በ2022/23 ውድድር ዘመን ከወጣው 2ነጥብ 7 ቢሊዮን ፓውንድ ቀጥሎ ከፍተኛው ነው፡፡

የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ቡድኖች በጥር በ2024 ያወጡት ወጪ ዝቅተኛ ቢኾንም የጣሊያን፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይ እና በስፔን ክለቦች ባለፈው ዓመት ካወጡት ገንዘብ የበለጠ ለዝውውር አውጥተዋል።

ዘጋቢ:- ሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here