ባሕር ዳር: ኅዳር 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ አስተናገጅነት ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ሁለተኛ ጨዋታ ዛሬ እየተካሄደ ይገኛል።
ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ያገናኘው ጨዋታ በኢትዮጵያ ፍጹም የበላይነት ተጠናቅቋል።
ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን ማሸነፍ የቻለችው 4 ለ 1 በኾነ ውጤት ነው። በዚህ ጨዋታ ዳዊት ካሳው ሃትሪክ መሥራት ችሏል።
ለኢትዮጵያ የማሸነፊያ ግቦቹን ዳዊት ካሳው ሦሥት ኳሶችን መረብ ላይ ሲያሳርፍ እንየው ስለሽ አራተኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
የደቡብ ሱዳንን ብቸኛ ማስተዛዘኛ ግብ ፓኖም ጁዋ አስቆጥሯል።
ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ የሴካፋ ውድድር ላይ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሌሎች ጨዋታዎችም ቀጥለው ሲካሄዱ ሶማሊያ ከኬኒያ 10፡00፣ ሱዳን ከዩጋንዳ 11፡00 እና ታንዛኒያ ከጅቡቲ ምሽት 2፡00 ሰዓት ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



