በቻይና ቤጂንግ እና በኔዘርላንድስ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ።

0
46
ባሕር ዳር: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የወርቅ ደረጃ በተሰጠው የቻይና ቤጂንግ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶቹ በበላይነት አጠናቅቀዋል።
አትሌት መስታውት ፍቅሩ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በቀዳሚነት አጠናቅቃለች።
አትሌት ኩመሺ ሲጫላ በ2 ሰዓት 24 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ሁለተኛ ስትወጣ አትሌት አንቻለም ሃይማኖት በ2 ሰዓት 24 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ሦሥተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን አጠናቅቃለች።
በወንዶች አትሌት ብርሃነ ጸጋዬ በ2 ሰዓት ከ13 ደቂቃ ሦሥተኛ ወጥቷል።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በኔዘርላንድስ በተካሄደ የ15 ኪሎሜትር የጎዳና ሩጫ በሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
አትሌት አስማረች አንለይ በ47 ደቂቃ 05 ሰከንድ ስታሸንፍ አትሌት አይናዲስ መብራቱ በ47 ደቂቃ 09 ሰከንድ ሦሥተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቅቃለች።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here