ባሕር ዳር: ኅዳር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ መድን መካከል ይደረጋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአራት ጨዋታዎች ሦሥቱን አሸንፎ በአንዱ ተሸንፎ ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ ስድስተኛ ላይ ይገኛል። የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ግን ከመሪው ሲዳማ ቡና በነጥብ እኩል እንዲኾን ያደርገዋል።
የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን እስካሁን ሦሥት ጨዋታዎችን ያደረገ ሲኾን በ5 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቀን 9 ሰዓት የሚደረገው ይህ ጨዋታ አሸናፊው ቡድን ጠንካራ ፉክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን



