በኢትዮጵያ ዋንጫ በርከት ያሉ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

0
52
ባሕር ዳር: ኅዳር 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬም በሃዋሳ፣ በአዲስ አበባ እና በጅማ ስታዲየሞች ቀጥለው ይውላሉ።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጠዋት 4:00 ላይ መቀሌ 70 እንደርታ ከፋሲል ከተማ ይጫወታሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ በተመሳሳይ ጠዋት 4:00 ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከነገሌ አርሲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሌላው ጨዋታ በጅማ ስታዲየም ጠዋት 4:00 ሃላባ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ የሚያደርጉት ነው።
በሃዋሳ ሰው ሠራሽ ሳር በተነጠፈለት ስታዲየም ምድረ ገነት ሽረ ከመቻል ይጫወታሉ።
ከሰዓት በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 7:00 ባሕር ዳር ከተማ ከሸገር ከተማ ሲጫወቱ በዚሁ ሜዳ ቀን 9:00 አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚገናኙ ይኾናል።
በጅማ ስታዲየም ደግሞ 7:00 ላይ ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ከአዲስ ከተማ እንዲኹም 9:00 ቢሸፍቱ ከተማ ከደሴ ከተማ ይገናኛሉ።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 7:00 ድሬዳዋ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ ሲገናኙ በዚሁ ሜዳ ቀን 9:00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ።
በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሳር የተነጠፈለት ሜዳ ላይ ቀን 7:00 ሐረር ከተማ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሲገናኙ ቀን 9:00 ላይ ደግሞ ንብ ከየካ ክፍለ ከተማ የሚጫወቱ ይኾናሉ።
ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወላይታ ድቻን 2ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል። በሌላ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአርባ ምንጭ ከተማ 5ለ4 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ኾኗል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here