ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አራተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ባርሴሎና ወደ ክለብ ብሩዥ ተጉዞ ጨዋታውን ያደርጋል። ባርሴሎና እስካሁን ከሦስት ጨዋታዎች ውስጥ በአንዱ ተሸንፎ በሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ በሻምፒዮንስ ሊጉ በ6 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።
ሁለቱ ክለቦች በሁሉም ውድድር እስካሁን አራት ጊዜ ተገናኝተው ሦስቱን ባርሴሎና በማሸነፍ የበላይነት አለው። አንዱ ጨዋታ ደግሞ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ሌሎች ጨዋታዎች ሲካሄዱ ፓፎስ ከቪያሪያል፣ ካራባግ ከቼልሲ በተመሳሳይ ሰዓት 2፡45 ይካሄዳሉ።
አያክስ ከጋላታሰራይ፣ ቤንፊካ ከባየር ሊቨርኩሰን፣ ኢንተር ሚላን ከካይራት አልማቲ፣ ማንቸስተር ሲቲ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ማርሴይ ከአታላንታ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ከአትሌቲክ ክለብ ጋር የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች 5፡00 ላይ ይካሄዳሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



