በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሦሥት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
7
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 4ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታ ዛሬ ሦሥት ጨዋታዎች ሲካሄዱ አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሸገር ከተማ፣ ሀዋሳ ላይ መቀለ 70 እንደርታ ከሀዋሳ ከተማ በተመሳሳይ 10፡00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ መድን 7፡00 ላይ የሚጫወቱ ይኾናል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን እና ነገሌ አርሲን 1ለ0 በማሸነፍ በሊጉ ከወዲሁ ጥንካሬውን እያሳየ የመጣ ክለብ ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በእያንዳንዱ ጨዋታ ግብ ማስቆጠሩ እንዳለ ኾኖ የግብ ማስቆጠር ምጣኔው ግን አነስተኛ ኾኖ ነው የተስተዋለው።
ተጋጣሚው ሸገር ከተማ በበኩሉ ከአዳማ ከተማ ጋር 0ለ0 ሲለያይ በኢትዮ ኤሌክትሪክ 1ለ0 የተሸነፈ ቡድን ነው። በዛሬውም ጨዋታ ቡድኑ ተጋጣሚው ጠንካራ በመኾኑ ጨዋታው ሊከብደው እንደሚችል ነው የሚጠበቀው።
ሀዋሳ ላይ መቀለ 70 እንደርታ ከሀዋሳ ከተማ ሌላው የዛሬው የሊጉ ጨዋታ ሲኾን ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ዲቻን 2ለ1፣ ድሬዳዋ ከተማን 2ለ0 ሲያሸንፍ በሲዳማ ቡና ደግሞ 1ለ0 ተሸንፏል።
ቡድኑ ዛሬ ለተጋጣሚው የተሻለ ጠንካራ ቡድን እንደሚኾን ነው የሚጠበቀው። በሌላ በኩል ተጋጣሚው መቀለ 70 እንደርታ ከመቻል ጋር 2ለ2 ሲለያይ በድሬዳዋ ከተማ 2ለ1 እና በምድረገነት 1ለ0 የተሸነፈ ቡድን ነው።
በዚህ ጨዋታ ካላቸው የሊጉ የማሸነፍ ጉዞ ሀዋሳ ከተማ የተሻለ ሊኾን እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ።
አዲስ አበባ ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ መድን 7፡00 የሚያደርጉት ሌላው የሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ ነው። ኢትዮጵያ መድን ከአዳማ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ያለ ግብ ነው የተለያየው።
ሁለት ጨዋታዎቹ የተራዘሙበት ኢትዮጵያ መድን በዛሬው ጨዋታ አሸንፎ ለመውጣት ጥረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ተጋጣሚው ሀድያ ሆሳዕና በበኩሉ ከአዳማ ከተማ እና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በነበረው ጨዋታ ያለ ግብ የተለያየ ሲኾን በባሕር ዳር ከተማ 3ለ1 የተሸነፈ ቡድን ነው።
በዛሬ ጨዋታው ታዲያ ያሉበትን ክፍተቶች በማረም አሸንፎ ለመውጣት ጥረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here