ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛው ዙር ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ከቦርንማውዝ ጋር ያገናኘው ጨዋታ በማንቸስተር ሲቲ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ማንቸስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ግቦቹን ሁለቱን ሃላንድ ሲያስቆጥር ቀሪዋን ኒኮ ኦሪሊ አስቆጥሯል።
የቦርንማውዝን የማስተዛዘኛ ብቸኛ ግብ አዳምስ አስቆጥሯል።
በሊጉ ሌላ ጨዋታ ዌስትሀም ኒውካስትልን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



