በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
104
ባሕር ዳር: ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት በመጨረሻ ቀን ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ድሬዳዋ ከተማ ከመቀለ 70 እንደርታ የሚያደርጉት ጨዋታ አንደኛው ሲኾን ሌላው አዳማ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ሌላው ጨዋታ ነው።
ድሬዳዋ ከተማ በአንደኛ ሳምንት ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ 2ለ0 ቢሸነፍም ያሉበትን ክፍተቶች በማረም በሁለተኛው ሳምንት ወላይታ ዲቻን በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተጭኖ በመጫዎት በአቤል ነጋሽ ግብ አሸንፎ ወጥቷል።
ተጋጣሚው መቀለ 70 አንደርታ በበኩሉ በአንደኛው ሳምንት በምድረገነት ሽረ 1ለ0 የተሸነፈ ሲኾን በሁለተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ከመቻል ጋር ተገናኝቶ 2ለ2 በኾነ ውጤት አቻ ተለያይቷል። ዛሬ ሦስት ነጥብ ለማግኘት ይጫወታል።
የቡድኑ ግብ አዳኝ ኪቲካ ጅማ እና ፍጹም አለሙ የተሻለ ግብ የማስቆጠር ብቃት እንዳላቸው የታየ ሲኾን ዛሬም ለተጋጣሚያቸው አስቸጋሪ እንደሚኾን ነው የሚጠበቀው። ጨዋታውም 10፡00 ላይ ይካሄዳል።
ሌላው በሊጉ የሚካሄደው ጨዋታ በአዳማ ከተማ እና በሀድያ ሆሳዕና መካከል የሚካሄድ ነው። አዳማ ከተማ በአንደኛው ሳምንት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ተገናኝቶ ያለ ግብ መለያየቱ ይታወሳል።
ቡድኑ በሁለተኛው ሳምንትም ከሸገር ከተማ ጋር ያለ ግብ ነው የተለያየው።
ተጋጣሚው ሀድያ ሆሳዕና በበኩሉ በመጀመሪያው ሳምንት በባሕር ዳር ከተማ 3ለ1 የተሸፈነ ሲኾን ሁለተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታም ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በነበረው ጨዋታ ያለ ግብ ነው የተለያየው።
የግብ ዕድል እየፈጠረ ያለው ጫላ ተሽታ በዛሬው ጨዋታ ለአዳማ ከተማ ተከላካዮች አስቸጋሪ እንደሚኾንም ይጠበቃል። ጨዋታውም 9፡00 ላይ ይካሄዳል።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here