ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሳምንቱ መጨረሻ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል የሚጠበቀው የሊቨርፑል እና የማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል።
እንዲጠበቅ ያደረገው ወቅታዊ ተቀራራቢ አቅም እና ብቃት ኖሯቸው ሳይኾን ታሪክ ነው፡፡ የሊጉ የምንጊዜም ስኬታማ ሁለቱ ክለቦች ናቸውና። ግንኙነታቸው በምንም ሁኔታ ውስጥ ሁሌም ይጠበቃል፡፡ የፕሪምየር ሊጉ ድረ ገጽ ጸሐፊ አድሪያን ክለርክ የስምንተኛ ሳምንት ግዙፉን ጨዋታ በቃኘበት ቅድመ ትንታኔው መግቢያ እንዲህ ይላል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ ከመጋቢት ወር ወዲህ ከሜዳው ውጭ ድል ማድረግ አልቻለም፡፡ ኾኖም ሊቨርፑል ሦስት ተከታታይ ጨዋታ የተሸነፈበት መንገድ ዩናይትድ ዕድሉን እንዲሞክር ያደርገዋል በማለት በጣቢያው ላይ አስፍሯል፡፡
ክላርክ የትኞቹ ተጨዋቾች የክለቦቻቸው ወሳኝ ሊኾኑ ይችላሉ ሲል ባነሳው ሃሳብ ከሊቨርፑል ኮዲ ጋክፖን አስቀድሟል፡፡
ቀያዮቹ 300 ሚሊዮን ፓውንድ ካወጡበት ዝውውር በላይ ጋክፖ ጥሩ አቅም ላይ ይገኛል ብሏል፡፡ ከፋሎረይን ቨርትዝ፣ ኢኪቲኬ እና አሌክሳንደር ኢሳቅ እንዲኹም ከወሳኙ ተጨዋች ሙሐመድ ሳላህ ለአርኔ ስሎት አቅም የኾነው ኮዲ ጋክፖ ነው፡፡
ጋክፖ በግብ ዕድል ፈጠራ ከተሻጋሪ ኳሶች መጠቀም በተቃራኒ የግብ ክልል ውስጥ ንክኪ በማድረግ እና በሙከራ ከየትኛውም የሊቨርፑል ተጨዋች የተሻለ ነው፡፡
ከፕሪምየር ሊግ ሌሎች ተጨዋቾች ጋር ሲነጻጸርም በቁጥር ብዙ አይበለጥም ንክኪዎችም ለከፋ የሚሰጡ አይደሉም ነው ያለው፡፡
በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል ቡሩኖ ፈርናንዴዝ አሁንም ቁልፉ ሰው ነው፡፡ ክለቡ ከውጤት ጋር ሲታገል እሱ ግን ነጥሮ የሚወጣው ተጨዋች ይኾናል፡፡ ቁጥሮች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው ብሏል፡፡
በግብ ዕድል ፈጠራ ከረጃጅም ኳሶች ወደ ክልል በሚወጡ ኳሶች ወደ ውጭ ቅጣት ክልል ውስጥ ኳስ ይዞ በመግባት ከየትኛውም የሊጉ ተጨዋች የበለጠ ቁጥር ላይ ይገኛል ነው ያለው፡፡
በሊቨርፑል በኩል አርኔስሎት የሙሐመድ ሰላህን ያለፉትን ዓመታት አቅም ዘንድሮ እያገኙ አይደለም፡፡ በተለይ በግብም ኾነ በግብ ዕድል ፈጠራ አመቻችቶ በማቀበል በአምናው እና በዘንድሮው መካከል ያለው ቁጥር አስደንጋጭ ልዩነት ላይ ይገኛል፡፡
ሆኖም ሳላህ ዩናይትድ ላይ ይጠነክራል፡፡ ካለፉት 11 ግንኙነቶች በ10ሩ ግብ አስቆጥሮበታልና ብሏል፡፡
ሳላህ በግብ ማስቆጠርም ኾነ በማመቻቸት እንደ ዩናይትድ የሚቀናው ክለብ የለም፡፡ 19 የግብ ተሳትፎ አድርጓልና፡፡ በማጥቃቱ ረገድ አሠልጣኖች አንዱ የሌላውን ዕቅድ ለማጥፋት ይሠራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚህ ሂደት ከኳስ ውጭ በፍጥነት በመሮጥ የሚታወቀው ብርያን ምቤሞው መጠንቀቅ የሊቨርፑል ተከላካዮች እጣ ይሆ ኾናል፡፡ ምቤሞው ከኩኛ፣ ፈርናንዲዝ አልያም ከሜሰን ማውንት ተሻጋሪ ኳስ ለመጠበቅ ከኳስ ውጭ ሲሮጥ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ይላል፡፡
በሊቨርፑል በኩል የቨርትዝ የማከፋፈል ችሎታ ይጠበቃል። ቨርትዝ ከተከላካይ አማካኞች ነጻ ኾኖ የሚቀበለውን ኳስ ለሳላህና ጋክፓ የማቀበል እይታው ተደንቆለታል፡፡ ምንም እንኳ የግብ ተሳትፎ እስካሁን ባይታይም ነው ያለው፡፡
የሁለቱ ክለቦች የመከላከል አቅም ሲፈተሸ ሁለቱም ክለቦች በቅርቡ ያሉበት የመከላል አቅም የሚተማመኑበት አልኾነም፡፡ ሊቨርፑል ለበርካታ ጊዜ በመጠቃት 10ኛ በመኾን የተዳከመ ሲኾን ዩናይትድም 16ኛ ላይ ይገኛል፡፡
አሊሰን፣ ኮናቴ፣ ግራቭንቦርች እና ዋታሩ አንዶ በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ ያልተመለከትናቸው ጉዳት ላይ የሚገኙ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ናቸው፡፡ አሁንም የቀያዮቹ ተስፋ ቨርጅል ቫንዳይክ ነው፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ በመከላከል ስህተት ግብ የሚቆጠርበት ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ከመከላከል ስህተት በተነሳ ኳስ ስድስት፣ ስድስት ተሞክሮባቸው ዩናይትድ ሦስት፣ ሊቨርፑል ሁለት ተቆጥሮባቸዋል፡፡
ይህ ከወቅታዊ ተፎካካሪነት ይልቅ ታሪክ ያገዘፈው ጨዋታ ምሽት 12፡30 ይጀምራል።
በእርስዎ ግምት ድል ለሊቨርፑል ወይስ ለዩናይትድ?
ዘጋቢ:- ግርማ ሞገስ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን