ዋልያዎቹ ለክብር ቡርኪናዎች ደግሞ የዓለም ዋንጫውን ትኬት ለመውሰድ ዛሬ ይፋለማሉ።

0
60
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዋልያዎቹ ምንም እንኳን ከዓለም ዋንጫው የተሰናበቱ ቢኾንም ዛሬ የመርሐ ግብር ማሟያ እና ለሀገራቸው ክብርም ወደ ቡርኪነፋሶ አቅንተው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫው ከተሰናበተ ወዲህ የሚያደርገው የመርሐ ግብር ማሟያ ጨዋታው ነው።
ቡድኑ ከሦስት ቀን በፊት ከጊኒ ጋር ባደረገው የመርሐ ግብር ማሟያ ጨዋታ ጊኒን 1ለ0 ማሸነፍ መቻሉ በቡድኑ ላይ ጥሩ መነሳሳትን ፈጥሯል።
ምንም እንኳን ዋሊያዎቹ ይህ ጨዋታ ነጥቡ ባይጠቅማቸውም በታሪክ መዝገብ ላይ ለሚያስቀምጡት ውጤት ግን ወሳኝ ይኾናል።
ምድብ አንድ ላይ የሚገኙት ዋሊያዋቹ እስካሁን ካደረጓቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ውስጥ 2ቱን አሸንፈው 3 ጊዜ አቻ ሲለያዩ ቀሪውን ደግሞ ተሸንፈዋል። በዚህም 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ዋልያዎቹ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሜዳው ኡጋዱጉ ስታዲም ላይ የሚገጥሙት የቡርኪነፋሶ ቡድን ቀላል የሚባል አይደለም። በደረጃም በ18 ነጥብ ሠብሥቦ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ቡድን ነው።
ከዚህ ቡድን ግብጽ ቀድማ ማለፏን አረጋግጣለች።
ዛሬ ዋሊያዎቹ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑበት ዋጋድጉ ስታዲየም 29 ሺህ 800 ተመልካች የሚይዝ ሲኾን እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር 1981 ተጀምሮ 1984 ነው ያለቀው። ይህ ስታዲየም 1996 የዕድሳት ሥራ ተሠርቶለትም ነበር።
መልካም ዕድል ለዋሊያዎቹ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here