ባሕር ዳር ፡መስከረም 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ትልልቅ ክለቦች ነጥቦችን በመሠብሠብ የሊጉን ፉክክር አጠናክረዋል።
ማንቸስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
አስቶን ቪላ በሜዳው በርንሌይን 2ለ1 ሲረታ፣ ኤቨርተን ደግሞ ክሪስታል ፓላስን በተመሳሳይ 2ለ1 ረቷል።
ኒውካስትል ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ባደረገው ጨዋታ 2ለ0 አሸናፊ ኾኗል።
በሌላ ጨዋታ ደግሞ ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ከብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን ጋር 1ለ1 በኾነ ውጤት ተለያይተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!