የሁለቱ ሚላኖች ሜዳ ሳንሴሮ ሊፈርስ ነው።

0
27
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን በ1926 የተገነባው ሳንሴሮ ስታዲየም በፋሽን ከተማዋ ሚላን ከሴሪ ኤ ጨዋታዎች ማከናወኛነት ባሻገር እንደ አንድ የቱሪስት መስህብ ኾኖ ያገለግላል።
ውጤታማዎቹ ኤሲ ሚላን እና ኢንተር ሚላን የሳንሴሮ ስታዲየምን በጋራ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
ይህ ዕድሜ ጠገብ ስታዲየም በሌላ አዲስ ስታዲየም ሊተካ ነው ተብሏል።
ሁለቱ የሚላን ከተማ ክለቦች ከ2030 ጀምሮ የሚገለገሉበት እጅግ ዘመናዊ እና አዲስ ስታዲየም ገንብተው ለማጠናቀቅ ሥራ ላይ ናቸው።
በ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዩሮ የሚገነባው አዲሱ ስታዲየም ከ72 ሺህ በላይ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል ተብሏል።
ዕድሜ ጠገቡ ሳንሴሮ ስታዲየም 100ኛ ዓመቱን ሲደፍን እድሳት አይጠብቀውም ወይም ወደ ሙዚየምነትም አይቀየርም እጣ ፋንታው መፍረስ ብቻ እንደኾነ ነው የተገለጸው።
ታሪካዊው የሳንሴሮ ስታዲየም ኤሲ ሚላን ባለሜዳ ሲኾን ሳንሴሮ ተብሎ ይጠራል። በአንጻሩ ኢንተር ባለሜዳ ሲኾን ጁሴፔ ሜኤዛ በሚል ስያሜ እየተጠቀሙበት አንድ ምዕተ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል።
በመልሰው ጥበቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here