ወሳኙ ጨዋታ በሴንት ጄምስ ፓርክ ስታዲየም

0
53
ባሕር ዳር: መስከረም 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ኒውካስትል ዩናይትድን የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ትናንት ክሪስታል ፖላስ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 ማሸነፉን ተከትሎ የሁለተኛ ደረጃን ከአርሰናል መረከቡ ይታወቃል። አርሰናል አሁን በ10 ነጥብ ወደ ሰባተኛ ደረጃ ተንሸራትቷል። በመኾኑም የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ክሪስታል ፖላስን በአንድ ነጥብ በመብለጥ የተነጠቀውን የሁለተኛ ደረጃ የሚያስመለስ ይኾናል። ስለኾነም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ በእጅጉ ተጠባቂ አድርጎታል።
በአርሰናል በኩል በጉዳት ከጨዋታ ርቆ የቆየው ማርቲን ኦዴጋርድ የሚሰለፍ መኾኑም ተነግሯል። ኒውካስትል ዩናይትድ በአንጻሩ እስካሁን ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው። በሦስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቶ እና በአንዱ አሸንፎ በስድስት ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።ኒውካስትል በሜዳው ከአርሰናል ጋር ያደረጋቸውን ያለፉትን ሦስት የቅርብ ጊዜ ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት ማሸነፉ ዛሬም ለአርሰናል ፈተና ይኾንበታል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
በኒውካስትል በኩል አንቶኒ ጎርደን ከቅጣት ተመልሶ የሚጫዎት ይኾናል። ጨዋታው በሴንት ጄምስ ፓርክ ስታዲየም ምሽት 12:30 ሰዓት ይካሄዳል።ቀን 10፡00 ሰዓት ወራጅ ቀጣና ውስጥ ያለው አስቶን ቪላ በሜዳው ቪላ ፓርክ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ፉልሃም ይጫወታል።
ዘጋቢ:- ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here