“በውጤቱ ሕዝቡን ይቅርታ እንጠይቃለን” ስለሺ ስህን

0
19
ባሕር ዳር፡ መስከረም 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በቶኪዮ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበውን ውጤት በተመለከተ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚመጥን አይደለም ብሏል። ፕሬዚደንቱ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተመዘገበው ውጤት ሕዝቡን ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል። በቶኪዮ ዓለም ሻምፒዮና ለተመዘገበው ደካማ ውጤት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችንም ፕሬዚደንቱ አትሌት ስለሺ ስህን ገልጿል።
ለሻምፒዮናው በተደረገው ዝግጅት አሠልጣኞች በጋራ እና ትብብር የመስራት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ፕሬዚዳንቱ ይፋ አድርጓል። በተለይ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር አለመተባበሩ በግልጽ ይታይ ነበር ያለው ኮማንደር ስለሺ ስህን ለማስተካከል ሙከራዎች ቢደረጉም በሚፈለገው ልክ አልሆኑም ብሏል።
አሠልጣኞች አትሌቶቻቸውን በግል የማሠራት ፍላጎት ማሳየታቸው ሀገርን ዋጋ እንዳስከፈለ ፕሬዚደንቱ ገልጿል። ኮማንደር ስለሺ ስህን በሁሉም ባይሆን በቡድን አባላቱ መካከል ሀገራዊ ስሜቱም በሚጠበቀው ልክ እንዳልነበር አሳውቋል። በመድረኩ በ35 አትሌቶች የተወከለችው ኢትዮጵያ በሁለት ብር እና በሁለት የነሃስ ሜዳልያ ከዓለም 22ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here