በዓለም የእግር ኳስ ሽልማት ከፍተኛው እንደኾነ የሚነገርለት የባላንዶር የሽልማት ሥነ ሥርዓት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ተካሂዷል።
በዚህ ሥነ ሥርዓት የዓለም ምርጦች ተመርጠዋል።

ኦስማን ዴንበሌ የባላንዶር አሸፊ ኾኗል።

አይታና ቦንማቲ ደግሞ በሴቶች የባላንዶር አሸናፊ ኾናለች።

ላሚን ያማል የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋቾች ተብሎ ተመርጧል።

በሴቶች ቪኪ ሎፔዝ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ተብላ ተመርጣለች።

ሳሪና ዊግማን በሴቶች የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ ተሰኝተዋል።

ሊዊስ ኤንሪኬ በወንዶች የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለዋል።

ጂያንሉጂ ዶናሩማ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ተብሏል።

በሴቶች ደግሞ እንግሊዛዊቷ ሃናህ ሃምፕተን ምርጥ ግብ ጠባቂ ተብላለች።

በወንዶች ቪክቶር ዮከሬሽን የዓመቱ ምርጥ አጥቂ ተብሏል።

በሴቶች ኢዋ ፓጆር ምርጥ አጥቂ ተብላለች።

የአርሰናል የሴቶች ክለብ የዓመቱ ምርጥ ክለብ ተብሏል።

በወንዶች ደግሞ ፒኤስጂ የዓመቱ ምርጥ ክለብ ተብሏል።