በዓለም የእግር ኳስ ሽልማት ከፍተኛው እንደኾነ የሚነገርለት የባላንዶር የሽልማት ሥነ ሥርዓት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እየተካሄደ ነው።
የአርሰናሉ አጥቂ ቪክቶር ዮከሬሽ የዓመቱ ምርጥ አጥቂ ተሰኝቷል።
አጥቂው በ204/25 የውድድር ዘመን በፖርቱጋሉ ሰፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ድንቅ ጊዜን አሳልፏል። በ52 ጨዋታዎች 54 ግቦችን በማስቆጠር ድንቅ የውድድር ጊዜ ነበረው።
በሴቶች ደግሞ የባርሴሎናዋ አጥቂ ኢዋ ፓጆር አሸናፊ ኾናለች።