የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ በተጠባቂ ጨዋታዎች ይመለሳል።

0
7
ባሕር ዳር፡ መስከረም 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሀገራት ጨዋታ ምክንያት የተቋረጠው የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ሲመለስ ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በዛሬው ጨዋታ ትኩረት ያገኘው 8፡30 ላይ የሚካሄደው አርሰናል ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።
በሦሥተኛ ሳምንት በሊቨርፑል 1ለ0 የተሸነፈው አርሰናል ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር በሜዳው ይጫወታል።
ክለቡ ከፎረስት ጋር ባለፉት ጊዜያት ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች የበላይነት አለው።
ከ1989 ወዲህ ፎረስትን በራሱ ሜዳ 14 ጊዜ ገጥሞ ያልተሸነፈው አርሰናል ዛሬስ ታሪኩን አስጠብቆ ይቀጥል ይኾን ? የሚለው ይጠበቃል።
ኖቲንግሃም ፎረስት በፕሪምዬር ሊጉ ከአርሰናል ጋር ከተጫወታቸው 16 ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ነው ያሸነፈው።
በቅርቡ ፖስቴኮግሉን የሾመው ኖቲንግሃም ፎረስት በአዲሱ አሠልጣኝ እየተመራ የዛሬውን ጨዋታ ያደርጋል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስትል ከዎልቭስ፣ ፉልሀም ከሊድስ ዩናይትድ፣ ኤቨርተን ከአስቶን ቪላ፣ ፓላስ ከሰንደርላንድ እና ቦርንማውዝ ከብራይተን ይገናኛሉ። ሁሉም ጨዋታዎች ቀን 11፡00 ይደረጋሉ፡፡ ምሽት 1፡30 ዌስትሃም ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐር እና ብሬንትፎርድ ከቼልሲ ምሽት 4፡00 ላይ ይጫዎታሉ።
ዘጋቢ:- ምስጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here