አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች-ከአሚኮ

0
5
ባሕር ዳር፡ መስከረም 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
👉20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ በጃፓን ቶኪዮ ይጀመራል። ኢትዮጵያ በ36 አትሌቶች በተለያዩ የአትሌቲክስ ርቀቶች የምተሳተፍ ይኾናል።
👉ነገ በሚጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 196 ሀገራት ይሳተፋሉ። ውድድሩ ለዘጠኝ ቀናት በቶኪዮ ይካሄዳል።
👉በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የማንቸስተር ደርቢ በጉጉት ይጠበቃል። ፕሪምየር ሊጉ ከሀገራት ጨዋታ መልስ ነገ ይጀምራል። በሳምንቱ ከሚካሄዱ ጨዋታዎች መካከል የማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። ጨዋታው እሑድ ምሽት 12:30 ይጀምራል።
👉ማንቸስተር ዩናይትድ የገንዘብ ክፍተቱን ለመሙላት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሊያዘጋጅ ነው።
ማንቸስተር ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን የአውሮፓ ውድድሮች ላይ ባለመሳተፉ የገንዘብ እጥረት ሊገጥመው ይችላል ነው የተባለው።
👉የቼልሲው አጥቂ ዴላፕ እስከ መጭው ታህሳስ ድረስ በጉዳት ከሜዳ እንደሚርቅ ቢቢሲ አስነብቧል። ተጫዋቹ ቼልሲ ከፍልሃም ጋር በነበረው ጨዋታ መጎዳቱ ይታወሳል።
👉አርሰናል የዊሊያም ሳሊባን ውል ለማራዘም እንቅስቃሴ ጀምሯል። የተጫዋቹ የኤምሬትስ ቆይታ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን በ2027 ይጠናቀቃል።
ይህን ተከትሎ አርሰናል የተጫዋቹን ውል በአምስት ዓመት ለማራዘም እየሠራ ነው። ሪያል ማድሪድ የሳሊባ ፈላጊ ሲኾን በውል ማራዘሙ ዙሪያ የተከላካዩ ሃሳብ አልታወቀም።
ክለቡ ይህን ክፍተት ለመሙላት በሳምንቱ አጋማሽ ከሌሎች የአውሮፓ ክለቦች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት እያሰበ እንደኾነ ተገልጿል።
👉 ዌስትሃም ከቶተንሃም በሚያደርጉት የለንደን ደርቢ የሁለቱንም ክለቦች ምስል (“Half-and-half”) ሹራብን እንዳይለብሱ ተከልክሏል።
ዌስትሃም ከቶተንሃም ጋር በሚያደርገው የለንደን ደርቢ ደጋፊዎች ሁለቱንም ክለቦች በአንድ አሠርተው የሚለብሱ ደጋፊዎች ናቸው የተከለከሉት።
የደኅንነት ስጋቶችን ለመቀነስ እና የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊዎች በተገቢው ቦታ መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ወሳኔው እንደተላለፈ ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here