ባሕር ዳር: ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ሲቲ ጣልያንዊውን ግብ ጠባቂ ጃንሉጂ ዶናሩማን ለማስፈረም ተስማምቷል።
ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤሰጂ ጋር እንደማይቀጥል የተነገረው ዶናሩማ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቆይቷል። በመጨረሻም ለማንቸስተር ሲቲ ለመጫወት መስማማቱን ፋብሪዚዮ ሮማኖ አስነብቧል። ሊጠናቀቅ በተቃረበው የዝውውር ወቅት በርከት ያሉ ዝውውሮች እየተፈጸሙ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ አንቶኒን ለሪያል ቤቲስ ለመሸጥ ተስማምቷል። ጁቬንቱስ ደግሞ አጥቂውን ሎኢስ ኦፔንዳን ከአሪ ቢ ሊብዚንግ ለማስፈረም መስማማቱ ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን