ባሕር ዳር: ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 2025/2026 የውድድር ዘመን ሦስተኛ ሳምንት ዛሬ ሲቀጥል ስድስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ዛሬ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሊጉ ባደረገው ጨዋታ ከድል ጋር መገናኘት ያልቻለው ማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ የሚጫወት ይኾናል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልድ ትራፎርድ ጨዋታውን ሲያደርግ ይህን ጨዋታ ማሸነፉ የውድድር ዘመኑን ለማስተካከል የሚያግዘው በመኾኑ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶታል።
ምንም እንኳን ዩናይትድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከድል ጋር መገናኘት ያልቻለ ቢኾንም ከአዲስ ቡድኖች ጋር ሲገናኝ ጥሩ ታሪክ ያለው ክለብ በመኾኑ ይህን ጨዋታ ለማሸነፍ እንደማይቸገር ነው እየተገለጸ ያለው። ክለቡ ከአዲስ ቡድኖች ጋር በተገናኘበት የመጨረሻዎቹ 23 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በአንዱም አልተሸነፈም።
በሌላ በኩል በርንሌይ ከሰንደርላንድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ድልን መቀዳጀቱ ለዛሬው ጨዋታ በጥሩ የሥነ ልቦና ግንባታ ላይ ኾኖ ነው ወደ ሜዳ የሚገባው።
ክለቡ ምንም እንኳን በሰው ሜዳ ላይ የሚጫዎት ቢኾንም ዩናይትድ ላይ ያለው ከፍተኛ ጫና ሊያግዘው እንደሚችል ነው የሚገመተው።
ሁለቱ ክለቦች ከዚህ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ በኦልድ ትራፎርድ የተገናኙበት ጨዋታ በአቻ ውጤት 1ለ1 ነበር መጠናቀቅ የቻለው ዛሬስ የሚለው የሚጠበቅ ነው።
ዩናይትድ ወደ መልካም አቋሙ ይመለሳል ወይስ የበርንሌይ አሠልጣኝ ስኮት ፓርከር በኦልድ ትራፎርድ ላይ በቅርብ ጊዜ የነበራቸውን ስኬት ይቀጥላሉ የሚለው ይጠበቃል። ጨዋታውም ቀን
11፡00 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
ሌሎች ጨዋታዎችም ሲቀጥሉ፦





ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!