አጫጭር የዝውውር ዜናዎች ከአሚኮ፦

0
73
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሊቨርፑል የአሌክሳንደር ኢሳክን ዝውውር እውን ለማድረግ አሁንም ጥረት ላይ ነው። ኒውካስትል እና ኢሳክ ባለመግባባታቸው እንደቀጠሉ ናቸው። ቢቢሲ በስፖርት ገጹ ሊቨርፑል አሁንም ስዊድናዊን አጥቂ ለማስፈረም እየሠራ መኾኑን ዘግቧል።
👉ክርስቶፎር ኑኩኩ ኤሲሚላንን ለመቀላቀል መስማማቱን ጎል አስነብቧል። ኑኩኩ ብዙ ተስፋ ተደርጎበት ለቼልሲ መፈረሙ ይታወሳል። ነገር ግን ፈረንሳዊ አጥቂ በሰማያዊዮቹ ቤት በልኩ ሳይገኝ አሁን መውጫ በር ላይ ተገኝቷል።
👉አሊሀንድሮ ጋርናቾ የቼልሲ ንብረት ሊኾን ስለመቃረቡ የጻፈው ደግሞ ደይሊ ሜል ነው። ተጫዋቹ በግል ቼልሲን ለመቀላቀል ዝግጁ ሲኾን ዩናይትድ እና ቼልሲ በዝውውር ገንዘቡ ገና አልተሰማሙም።
👉የክርስቲያል ፓላሱ ዋርተን በሪያል ማድሪድ እየተፈለገ ነው። እንደ አስ መረጃ ከኾነ የአሎንሶው ቡድን ዳኒ ሲባዮስ ክለቡን ለመልቀቅ በመፈለጉ ተተኪው እንዲኾን ነው ዋርተንን የሚፈልገው።
👉አርሰናል በሂንካፔ ዝውውር ዙሪያ ከባየር ሊቨርኩሰን ጋር በቀጥታ ንግግር እያደረገ ነው። ኢኳዶሯዊ ተከላካይ የዝውውሩ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት አርሰናልን የመቀላቀል እድሉ ሰፊ ነው ብሏል ጎል በዘገባው።
👉ጁቬንቱስ ኮሎ ሞዋኒን ለማስፈረም ተስማምቷል። በጎል መረጃ መሠረት ጁቬ ለፒኤስጂ 51 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ተስማምቷል።
👉አድሬ ኦናና ከማንቸስተር ዩናይትድ የመውጣት ፍላጎት እንደሌለው ፋብሪዚዮ ጽፏል። ኦናና በዩናይትድ በሚሠራቸው ስህተቶች ተደጋጋሚ ትችት እያስተናገደ ነው። ይህን ተከትሎ ተጫዋቹ በውሰት ወደሌላ ክለብ ሊያመራ እንደሚችል እየተወራ ነው። ኦናና ግን ዩናይትድን እንደማይለቅ አሳውቋል።
👉ዣቪ ሲሞንስ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ለንደን ይገኛል። ቼልሲ እና ቶትንሃም የሲሞንስ ፈላጊዎች ናቸው። ከሁለቱ የለንደን ክለቦች ለየትኛው ይፈርማል የሚለውም እየተጠበቀ ነው።
👉ሪያል ማድሪድ ኮቢ ማይኑን ለማስፈረም ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ፉክክር ውስጥ ገብቷል። ማይኑ በአሠልጣኝ አሞሪም ተመረጭ ባለመኾኑ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል የሜትሮ መረጃ ያሳያል።
👉ጆዜ ሞሪንሆ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ እያሰቡ መኾኑን ጎል አስነብቧል። አወዛጋቢው አሠልጣኝ ፌነርባቼን እየመሩ ነው። ነገር ግን ኖቲንግሃም ፎረስት ጆዜን አሠልጣኝ የማድረግ ሃሳብ አለው።
👉ማንቸስተር ዩናይትድ የሀሪ ማጉየርን ውል ለማራዘም ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ደግሞ ደይሊ ሜል አስነብቧል።
በአስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here