የለንደን ደርቢ ፍልሚያ ዛሬ በዌስትሃም እና ቼልሲ መካከል ይደረጋል።

0
88
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በመጀመሪያው የውድድር ሳምንት ሽንፈት የገጠመው ዌስትሃም ዩናይትድ ይህን ሽንፈት ለመቀየር ዛሬ ወደ ሜዳ ይገባል።
ዛሬ በለንደን በሚካሄደው የደርቢ ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት የተለያየውን የለንደን ተቀናቃኛቸውን ቼልሲን ነው የሚገጥሙት። በፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ተከታታይ የሽንፈት ታሪክ ያላቸው ዌስትሃም ዩናይትዶች በመጀመሪያው ጨዋታ በሰንደርላንድ 3 ለ 0 ተሸንፈዋል። የቡድኑ የሽንፈት ታሪክ አሁንም ለዘጠነኛ ጊዜ እንዳይደገም በአሠልጣኝ ግራሃም ፖተር ላይ ከፍተኛ ጫና ተፈጥሮባቸዋል። ግብ ጠባቂው ማድስ ሄርማንሰን በመጀመሪያ ጨዋታው ሦሥት ጎሎችን በማስተናገድ ደካማ ብቃት እንዳለው ታይቷል። ግብ ጠባቂው በፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ውስጥ ደካማው ግብ ጠባቂ ከሚባሉት ውስጥም ለመካተት ተገድዷል። የዌስት ሃም ዩናይትዱ ጃሮድ ቦወን ዛሬ የተሻለ ለቡድኑ ይሠራል ተብሎ ይጠበቃል።
ተጋጣሚው ቼልሲ በበኩሉ በመጀመሪያው ጨዋታ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያለግብ አቻ በተለያየበት ጨዋታ ደካማ የኾነው የአጥቂ ክፍሉ በግልጽ ታይቷል። በዚህ ጨዋታም 19 የግብ ሙከራዎች ቢኖራቸውም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ የቀሩ በመኾኑ በዚህ ጨዋታ ያላቸውን ብቃት አሻሽለው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ቼልሲዎቹ ምንም እንኳን ግብ ማስቆጠር ባይችሉም በጨዋታ የበላይ መኾናቸውን ግን አሳይተዋል። በመጀመሪያው ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታቸው 510 ኳሶችን ወደ ግብ ክልል ይዞ በመድረስ በሊጉ ከሊቨርፑል እና ከማንችስተር ሲቲ ቀጥሎ የተሻለ አቋም አሳይተዋል።
ቼልሲዎቹ የተከላካይ መስመራቸው ጠንካራ መኾኑ በዚህኛው ታይቷል፤ ይህም ለተቀናቃኛቸው ዛሬ አስቸጋሪ እንደሚኾን ነው የሚጠበቀው።
ከየካቲት 2023 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ በተከታታይ ሦሥት ጨዋታዎች ግብ አላስቆጠሩም። የቼልሲው ወጣቱ ኮከብ ኢስቴቫኦ በዚህኛው ጨዋታ ልዩነት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ተጫዋችም ነው። ሁለቱ ቡድኖች ካላቸው ታሪካዊ ግንኙነት አንጻር ሲታዩ ዌስትሃም በሜዳቸው ከቼልሲ ጋር ካደረጓቸው የመጨረሻ ስምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት አራት ጊዜ ብቻ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here