የርገን ክሎፕ ከሊቨርፑል አሠልጣኝነታቸው ሊለቁ ነው።

0
324

ባሕርዳር: ጥር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ስፖርት ሳይንስ ያጠኑት ጀርመናዊው የርገን ኖርበር ክሎፕ በ1972 በጋላተን ቡድን ጨዋታን በአጥቂ እና በተከላካይ ቦታ ጀምረው በሜንዝ አጠናቀዋል፡፡

በተጫዋችነታቸው በ325 ጨዋታዎች ተሰልፈውም 52 ግብ መረብ ላይ አሳርፈዋል፡፡

የርገን ክሎፕ አሠልጣኝነትን በሜንዝ ቡድን እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን 2001 ጀምረው ሊቨርፑል ላይ ደርሰዋል፡፡

እኝህ ጉምቱ ሰው በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከአሠልጣኝነታቸው ሊለቁ መኾኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ክሎፕ ሊቨርፑልን ማሠልጠን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ጥቅምት 2015 ሲኾን ውላቸው የሚጠናቀቀው ደግሞ በ2026 ነበር።

ሊቨርፑል በ2019 የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፏል፤ ከ30 ዓመታት በኋላም በ2019/20 የውድድር ዘመን የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ ማንሳትም ችሏል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here