ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ የ2025/2026 የውድድር ዘመን መክፈቻ ጨዋታ ላይ የዘር ጥቃት ያደረሰው ደጋፊ ተቀጥቷል።
ሊቨርፑል ከበርንማውዝ ጋር ባደረጉት የመክፈቻ ጨዋታ ላይ የበርንማውዙ አጥቂ አንትዋን ሴሜንዮ የዘር ጥቃት ተፈጽሞበታል። የዘር ጥቃቱን የፈጸመው አንድ የ47 ዓመት እንግሊዛዊ ደጋፊ ነበር። ይህ ደጋፊም ጥፋተኛ ኾኖ በመገኘቱ በሁሉም የእንግሊዝ እግር ኳስ ስታዲየሞች እንዳይገባ ታግዷል ነው የተባለው። ቢቢሲ እንደዘገበው ደጋፊው ከእግር ኳስ ስታዲየም በአንድ ማይል ርቀት ላይ እንዳይገኝም ታግዷል።
ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት ምርመራው እንደቀጠለ ነው። ከሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል። ተጨዋቹ የደረሰበትን የዘር ጥቃት ተከትሎ ጨዋታው 29ኛው ደቂቃ ላይ ለጥቂት ጊዜ እንዲቋረጥ ኾኖም ነበር። ውሳኔውን ተከትሎ ተጨዋቹ የተሰጠውን ፈጣን ፍትሕ አድንቋል። ፍትሕ እንዲያገኝ ለረዱት አካላትም ምሥጋና አቅርቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!