ሊቨርፑል የፕርሚየር ሊጉን መርሐ ግብር በድል ጀምሯል።

0
97
ባሕር ዳር: ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በወርሐ ሐምሌ ወሳኝ ተጫዋቻቸውን ዲያጎ ጆታ በድንገተኛ አደጋ ያጡት ሊቨርፑሎች የ2025/26 የውድድር ዘመን መርሐ ግብራቸውን በድል ጀምረዋል።
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ያለፈው ዓመት ሻምፒዮን ሊቨርፑል ከበርንማውዝ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4 ለ 2 በኾነ ውጤት አሸንፏል።በሜዳው አንፊልድ ሮድ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ሊቨርፑል የማሸነፊያ ግቦቹን ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ኮዲ ጋክፖ፣ ምሐመድ ሳላህ እና ፌዴሪኮ ኬሳ ማስቆጠር ችለዋል።
በርንማውዞችን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለት ግቦች አንቶይን ሴሜኒዮ ከመረብ አገናኝቷል። ግብጻዊው ሞሀመድ ሳላህ በተከታታይ 10 የፕርሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጨዋች በመኾን አዲስ ታሪክ ፅፏል። ኤኪቲኬ በሊቨርፑል ታሪክ በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታው ጎል አስቆጥሮ ለግብ የኾነ ኳስ ያመቻቸ ሁለተኛው ተጨዋች ኾኗል። ዳርዊን ኑኔዝ በ 2022 ፉልሀም ላይ ይህንን አድርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here