ፒኤስጂ የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን አሸነፈ።

0
59
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የአውሮፓ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን አሸንፏል። የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ፒኤስጂን ከኢሮፒያ ሊግ አሸናፊው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር አገናኝቷል። በጨዋታው ፒኤስጂ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ኾኗል።
አስቀድሞ ጨዋታውን 2 ለ0 መምራት የቻለው የእንግሊዙ ቶተንሀም በመጨረሻ ደቂቃዎች በተቆጠሩበት ግቦች ዋንጫውን ለማሸነፍ ተቃርቦ የነበረውን እድሉን አሳልፎ ሰጥቷል። መደበኛ የጨዋታ ሰዓታቸውን በአቻ ውጤት ያጠናቀቁት ሁለቱ ክለቦች አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት አምርተዋል። በተሰጠው መለያ ምት ፒኤስጂ 4 ለ3 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ኾኗል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here