አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች – ከአሚኮ

0
80
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 05/2017 ዓ.ም(አሚኮ) ዘቴሌግራፍ እንደዘገበው ሴኔጋላዊው አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰን በክረምቱ የዝውውር ወቅት ቼልሲን ለቆ ከወጣ ወደ ኒውካስትል ዩናይትድ ማምራት እንደሚመርጥ ተገልጿል።
✍️ ቼልሲ እና አርቢ ሌይፕዝሽ ሆላንዳዊውን አማካኝ ዣቪ ሲሞንስን ከፈረንሳዩ አጥቂ ክሪስቶፈር ንኩንኩ ጋር ለመለዋወጥ እየተነጋገሩ ነው ሲል ስካይ ስፖርት ጽፏል። ንኩንኩ ወደ ቀድሞ ክለቡ መመለስ የሚችልበት ሂደት ላይ መኾኑ ተዘግቧል፡፡
✍️ ሊቨርፑል የኒውካስትሉን አሌክሳንደር ኢሳክ ለማስፈረም ካልቻለ ዮአን ዊሳን ከብሬንትፎርድ ለማስፈረም እያሰበ ነው ሲል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡
✍️ ኮሎ ሙአኒ ከኒውካስትል ይልቅ ጁቬንቱስን መቀላቀል እንደሚመርጥ መናገሩን ቢልድ ኢን ጀርመን አስነብቧል።
✍️ ማንቸስተር ዩናይትድ የኤቨርተንን የቀድሞ አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት-ሌዊንን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም እያሰበ ነው።
✍️ የሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር የተባለው የባየር ሙኒኩን ፈረንሳዊ አጥቂ ኪንግስሊ ኮማን ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል ሲል የዘገበው ቶክ ስፖርት ነው።
✍️ ጃክ ግልሪሽ ከኤቨርተን ጋር ተስማምቷል። በማንቸስተር ሲቲ ቤት ቦታ እንደሌለው የተነገረው ጃክ ግልሪሽ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቆይቷል። ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንዳስነበበው ተጨዋቹ ለኤቨርተን ለመጫወት ተስማምቷል።
✍️ቶተነሀም ብራዚላዊውን የማንቸስተር ሲቲ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሳቫኒሆን ለማስፈረም እየተነጋገረ እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የ21 ዓመቱን ተጫዋች ለማዛወር ማንቸስተር ሲቲ 50 ሚሊዮን ዩሮ ጠይቋል፡፡
✍️የኢሲሚላኑ ተከላካይ ማሊክ ሶ ወደ ኒውካስትል ለመዛወር ተስማምቷል። ተጫዋቹን ለማስፈረም 34 ነጥብ 62 ዩሮ ተከፍሎበታል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here