በባሎን ዶር 2025 እጩዎች ፈረንሳያውያን እና እንግሊዝውያን የበላይነትን ይዘዋል።

0
69

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ2025 የባሎን ዶር ሽልማት እጩዎች ይፋ ሲደረጉ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ እያንዳንዳቸው በአራት ተጫዋቾች ከሌሎች ሀገራት በልጠው ቀርበዋል።

ፈረንሳይን ወክለው ሚካኤል ኦሊሴ፣ ኡስማን ዴምቤሌ ኪሊያን ምባፔ እና ዴሲሬ ዱዌ እጩ ኾነው ተመርጠዋል። እንግሊዝን ወክለው የቀረቡት ደግሞ ኮል ፓልመር፣ዴክላን ራይስ፣ ጁድ ቤሊንግሀም እና ሀሪ ኬን ናቸው። እነዚህ ሁለቱ ሀገራት በእጩዎች ብዛት መሪነቱን የያዙ ሲሆን ከእነዚህ ታላላቅ ተጨዋቾች መካከል የዘንድሮውን የባሎን ዶር አሸናፊ ማን ይወስዳል የሚለው ተጠባቂ ኾኗል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here