ማንቸስተር ዩናይትድ የስናፕ ድራጎን ዋንጫን አሸነፈ።

0
81
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቅድመ ውድድር የመጨረሻ ጨዋታውን በኦልድትራፎርድ ያደረገው ማንቸስተር ዩናይትድ ፊዮረንቲናን በማሸነፍ የስናፕ ድራጎን ዋንጫን አሸንፏል።
በመደበኛ የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 የተለያዩት ሁለቱ ክለቦች ወደ ፍጹም ቅጣት ምት አምርተው ዩናይትድ 5ለ4 በኾነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ድሉን ተከትሎ ማንቸስተር ዩናይትድ የስናፕ ድራጎን ካፕ አሸናፊ ኾኗል። ከጨዋታው በፊት ማንቸስተር ዩናይትድ በክረምት የዝውውር ወቅት ያስፈረማቸውን ተጨዋቾች በኦልድትራፎርድ አስተዋውቋል። ለቀድሞው ግብ ጠባቂው ዴቪድ ዴህያ ደግሞ ስጦታ አበርክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here