የ2025/26 የካፍ ኢንተር ክለብ ውድድሮች ድልድል ይፋ ኾነ።

0
42
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ2025/26 የካፍ ኢንተር ክለብ ውድድሮች ድልድል በታንዛኒያ ዳሬሰላም ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ወኪል ክለቦችም የመጀመሪያ ዙር ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል።
በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክለው ኢትዮጵያ መድን በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ከዛንዚባሩ ክለብ ምላንዴግ ጋር ተደልድሏል።
መድን የመጀመርያውን ጨዋታ በሜዳው የሚያደርግ ይኾናል። በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ካለፈ በሁለተኛው ዙር ከግብጹ ፒራሚድ እና ከሩዋንዳው ኤፒአር አሸናፊ ጋር ይገናኛል።
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ደግሞ ወላይታ ድቻ ወደፊት ከሚገለጽ የሊቢያ ክለብ ጋር ተደልድሏል። ወላይታ ድቻም የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳው የሚያደርግ ይኾናል። የመጀመሪያውን ዙር ማለፍ ከቻለ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከግብጹ አል-መስሪ ጋር ይጫወታል።
ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ከመስከረም 9/2018 ዓ.ም እስከ መሥከረም 18/2018 ዓ.ም የሚካሄዱ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here