ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንችስተር ዩናይትድ በአሜሪካ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሰመር ሲሪየስ ዋንጫ አንስቷል።
የቅድመ ውድድር ዝግጅት አካል ኾኖ አራት የእንግሊዝ ክለቦች በተሳተፉበት መድረክ ዩናይትድ በመጨረሻው ጨዋታ ከኤቨርተን ጋር 2 ለ 2 ተለያይቷል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ በብሩኖ ፈርናንዴዝ በ19ኛው ደቂቃ ላይ በፍጹም ቅጣት ምት መምራት ቢጀምርም የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው በ40ኛው ደቂቃ ላይ ኤቨርተን በኢሊማን ንዲያዬ አማካኝነት ግብ አሰሰቆጥሮ አቻ መኾን ችሏል።
ከእረፍት መልስ የተሻለ አጨዋወት በሁለቱም በኩል ከፈጣን የኳስ አጨዋወት ጋር ታይቷል። በማሰን ማውንት በ69ኛው ደቂቃ ላይ ለማንቸስተር ዩናይትድ አስቆጥሮ እንደገና መምራት ቢጀምርም ፈጣን የማጥቃት ጨዋታ የተጫዎተው ኤቨርተን ወደ ግብ የተሻገረች ኳስ በዩናይትድ ተጨዋች ተጨርፋ መረብ ላይ እንድታርፍ በማድረጋቸው አቻ ኾነው ጨዋታው ተጠናቅቋል።
ይሁን እንጅ ካደረጋቸው ሦሥት ጨዋታዎች ሁለቱን በማሸነፍ በአንዱ ነጥብ የተጋራው ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ የተዘጋጀውን ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡
በመርሴዲስ ቤንዝ ስታዲየም በተካሄደው የዌስትሃም እና የቦርንማውዝን ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ ቦርንማውዝን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል። የዌስትሃምን የማሸነፊያ ግቦች ኒክላስ ፉልከርግ በ24ኛው ደቂቃ እና ጃሮድ ቦወን በ67ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ዌስትሀም ዩናይትድ በ6 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን